JavaScript is required

ቀደም ብሎ የሚጀምር መዋዕለ ህፃናት (Early Start Kindergarten) - አማርኛ (Amharic)

ከስደተኛ ወይም ጥገኝነት ጠያቂ ዳራ ከሆኑ ቀደም ብሎ የሚጀምር መዋዕለ ህፃናት (Early Start Kindergarten (ESK)) ለማግኘት ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ። ኢኤስከይ (ESK) በየሳምንቱ ለልጅዎ የሚቻለውን ከፍተኛውን የነጻ መዋዕለ ህፃናትን ሰዓታት እንዲያገኙ ያግዝዎታል።

እንዴት ማመልከት እንደሚቻል

ኢኤስከይ (ESK) ብቃት ባለው መምህር በሚሰጡ ሁሉም የመዋዕለ ሕጻናት ፕሮግራሞች ይገኛል። በአቅራቢያዎ ያለ መዋዕለ ሕፃናትን በማነጋገር እና ቀደም ብሎ የሚጀምር መዋዕለ ሕጻናት የገንዘብ እርዳታን በመጠየቅ ልጅዎን ማስመዝገብ ይችላሉ። የመዋዕለ ሕፃናት አገልግሎቶች በቋንቋዎ እርስዎን ለመደገፍ ነፃ የትርጉም አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ።

እርዳታ ለማግኘት ወደ ትምሕርት መመሪያው የሶስት አመት እድሜ ልጆች የመዋዕለ ህጻናት መጠየቂያ መስመርን በስልክ 1800 338 663 ላይ መደወል ወይም የአካባቢዎ ምክር ቤት ማግኘት ይችላሉ። በቋንቋዎ እርዳታ ለማግኘት ወደ ብሄራዊ የትርጉም እና አስተርጓሚ አገልግሎት በስልክ 131 450 መደወል ይችላሉ፣ አስተርጓሚው ለአከባቢዎ ምክር ቤት ወይም የትምህርት መመሪያ ቁጥር እንዲደውሉ ይጠይቁት እና አስተርጓሚው በመስመር በመቆየት ያስተረጉምልዎታል።

መቼ ማመልከት እንደሚቻል

ህፃናት የሶስት አመት ህጻናት መዋእለ ሕፃናት ለመከታተል በተመዘገቡበት ዓመት ከኤፕሪል 30 በፊት ሶስት አመት ከሞላቸው ለኢኤስከይ (ESK) ብቁ ናቸው። 'መቼ መመዝገብ እንደሚቻል' ይመልከቱ።

ልጅዎ ከጃንዋሪ 1 እስከ ኤፕሪል 30 ባለው ጊዜ ውስጥ ከተወለደ የሶስት አመት ህጻናት መዋእለ ሕፃናትን በየትኛው አመት እንደሚጀምሩ መምረጥ ይችላሉ። ልጅዎ የሶስት አመት መዋእለ ሕፃናትን በሶስት አመት በሚሞላበት አመት ወይም አራት አመት ሲሞላቸው መጀመር ይችላል። ልጅዎ የሶስት አመት መዋእለ ሕፃናትን በሶስት አመት በሚሞላበት አመት ከጀመረ በ5 አመታቸው ትምህርት ይጀምራሉ። ልጅዎን በአራት አመታቸው በሚሞላበት አመት የሶስት አመት መዋእለ ሕፃናት ለመላክ ከመረጡ በስድስት አመታቸው ትምህርት ይጀምራሉ።

ልጅዎ ለኢኤስከይ (ESK) ብቁ በሚሆንበት ጊዜ ለማስላት እርዳታ ከፈለጉ፣ የትምህርት መምሪያን፣ የአካባቢ ምክር ቤትዎን፣ የወሊድ እና የሕጻናት ጤና ነርስዎን፣ ወይም በአካባቢዎ ያሉ መዋዕለ ሕፃናትን ወይም በአካባቢዎ ካሉት የሚከተሉትን ድርጅቶች ማነጋገር ይችላሉ፦

  • የሶስት ዓመት ህፃናት መዋእለ ሕጻናት መጠየቂያ መስመር 1800 338 663
  • ብራዘርሁድ ኦፍ ሰይንት ሎረንስ (Brotherhood of St Laurence) 03 9483 1183
  • ፋውንዴሽን ሃውስ (Foundation House) 03 9389 8900
  • ኤፍካ የህጻናት አገልግሎት (Fka Children’s Services) 03 9428 4471
  • ቪክሴግ ኒው ፊቸርስ (VICSEG New Futures) 03 9383 2533

ልጄ የአራት አመት ህጻናት ትምህርት ቤት መሄድ አለባት/አለበት?

አዎን፣ ቀደም ብሎ የሚጀምር መዋዕለ ህጻናት ፕሮግራምን የተጠቀሙ ህጻናት ነጻ ወይም አነስተኛ ወጪ ላለው የአራት አመት ህጻናት ትምህርት ቤትም ብቁ ናቸው። የአራት አመት መዋእለ ሕፃናት ከ2025 ጀምሮ በሂደት ወደ ቅድመ ዝግጅት ትምህርት/Pre-Prep እየተቀየረ ነው። በ2026፣ የሚከተሉት ህጻናት በሳምንት እስከ 25 ሰአታት የሚደርስ የቅድመ ዝግጅት ትምህርት/Pre-Prep እድል ያገኛሉ፦

  • ከስደተኛ ወይም ጥገኝነት ጠያቂ ዳራ ለመጡ
  • እንደ አቦርጂናል እና/ወይም የቶረስ ስትሬት አይላንደር ነን ለሚሉ
  • ቤተሰባቸው ከልጆች ጥበቃ ድርጅት ጋር ግንኙነት ለነበራቸው

ባለፈው አመት በESK በኩል መመዝገብ ልጅዎ በቪክቶሪያ የትም ቢኖሩ የቅድመ ዝግጅት ትምህርት/Pre-Prepን የሰዓት ብዛት በየሳምንቱ እንዲያገኙ ዋስትና ይሰጣል። ቤተሰቦች ባለፈው አመት በESK ባይመዘገቡም ለቅድመ ዝግጅት ትምህርት/Pre-Prep ብቁ ይሆናሉ።

Updated